እግዝእትነ ማርያም
ምስለ ፍቁር ወልዳ።

አማርኛDeutschEnglish

መስቀል ቤዛነ

ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ኦፕፊኮን ፣ ዙሪክ ፣ ስዊስ (ስዊዝርላንድ)

Debre Gennet Qiddist Maryam
Äthiopisch-Orthodoxe Tewahedo Kirche
Opfikon, Zürich, Schweiz

Debre Gennet Qiddist Maryam
Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
Opfikon, Zurich, Switzerland

   ()
   የሚቀጥለው ቅዳሴ: >>> (Sunday, December 18, 2011, 9 am Ethiopian Liturgy celebrated in the Wasserkirche in Central Zurich)
  በዚህ ክፍል >

 

ኅዳር ፯, 2004  
የደመራ መዓል በስዊዘርላንድ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

የዘንድሮው የ 2004 ዓ.ም. የደመራ በዓል እንደተለመደው ኦፕፊኮን ዙሪክ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከመላው ስዊዘርላንድና አጎራባች አገሮች በተሰበሰቡ ምእመናንና ምእመናት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል:: የደመራውን አክባበር አርቲስት ተስፉ ወልደ ሥላሴ  ከታች እንደሚታየው በፎቶ ማንሻው ቀርጾታል::

ሥዕላት / ፎቶ >


ነሐሴ ፲፪, 2002  
የዙሪክ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያምን ምስረታ 10ኛ ዓመት

የዙሪክ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያምን ምስረታ 10ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ነሐሴ 16 ቀን (22.08.2010)
በ ቬቲኮን ( Zürich-Witikon)ከጧቱ 12 ሰዓት (6:00 AM)በቅዳሴ የሚጀምር ታላቅ ዝግጅት ይጠብቃችኋል::
የእለቱ መርሃ ግብር ቅዳሴ - መዝሙር- ወረብ -ስብከትን ያካተተ ከመሆኑም በላይ የተጋበዙ እንግዶች ስለበዓሉ ንግግር ያደርጋሉ::
ከእንግዶቹም መሃል የታሪክ ምሑርና የባለ ብዙ መጽሐፍት ደራሲ የሆኑት ክቡር ልኡል (ዶክተር) አስፋወሰን አስራተ አንዱ ሲሆኑ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማቋቋም ትልቅ አስተዋጽዖ የነበረውና የዛሬው የእንግሊዝ ሀገር ነዋሪ የሆነው ዲያቆን መኮንን ግርማም ከሰባክያኑ አንዱ ነው:: በዚህ ታሪካዊ ቀን ተገኝተው የበረከቱ ተሳታፊ ለመሆን በወቅቱ እንዲገኙ ቤተ ክርስቲያኒቱ ጥሪዋን ታቀርባለች:: አድራሻውንና በሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች ለሚጠቀሙ ሙሉ መረጃው ከዚህ ስር ይገኛል::

PDF >


የካቲት ፳፬, 2002  
ጾም ማለት የምግብ ለውጥ ማድረግ ብቻ ነውን?
በዚህ በጀመርነው የአቢይ ጾም ወቅት ለጿሚው አዳጋች የሚባለው "የጾም ምግብ" በቀላሉ አለማግኘት ነው ይባላል:: ብዙዎች አሣም ደም አለውና አይበላም ይላሉ:: የጾሙ ከፍስኩ እንዳይነካካ ብርቱ ጥንቃቄ የሚያደርጉም ጿሚዎች ቁጥር የሚናቅ አይደለም:: በዚህ በስደት ዓለሙም ቢሆን በተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ከተደነገጉት ሰባቱ አጽዋማት መካከል የአቢይ / ሁዳዴ ጾምን አብዛኛዎቹ አማንያን ይጾሙታል:: የምግብ ለውጥ ይደረጋል ማለት ነው::

ያንብቡ ›

 
የካቲት ፲፰, 2002  
ስለ ቤተ ክርስቲያናችን

በስዊዘርላንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ኦፕፊኮን / ዙሪክ ውስጥ በ1992 ዓ.ም. (እ.አ.አ.2000) ተመስረተች::

ያንብቡ ›

 
 
 
 
 

በዓላት - ዝግጅቶች

>>>

 

 

 

 

 

 

 

 
   
ግጻዌ

 
ምንጭ
Join our mailing list and receive e-mails about news and updates